Latest

የሽግግር ብዥታ፣ ሥርዓት አልበኝነትና ሥጋቶች - መንግሥቱ አሰፋ

የሽግግር ብዥታ፣ ሥርዓት አልበኝነትና ሥጋቶች - መንግሥቱ አሰፋ

አሁን ባለንበት የሃገራችን ጉዳይ ሥርዓት አልበኝነት ትልቁ ችግር እንደሆነ ይታያል። ይህ በራሱ ትክክለኛ “ትልቁ ችግር” ነው ወይ የሚለው ጥያቄ እምደተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉትን ጥቂት ሐሳቦች ላስቀምጥ።

እየተካሄደ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ “የሥርዓት ለውጥ” ነው ለማለት እደፍራለሁ። በፖለቲካ ፓርቲው (ኢሕአዴግ) የረጅም ጊዜ executive monopoly, culture and modus operandi ፈተና የገጠመው ይመስላል። 

በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠረው የለውጥ ቡድን ማኅበራዊ መሠረቱ ትልቅ ቢሆንም ለበለጠ ዘላቂ ቅቡልነት እና ተዓማኒነት (lasting legitimacy and trust) ግን ሕጋዊ ማዕቀፍና እና መዋቅራዊ ቁመና ( legal framework and structural strength) ያስፈልገዋል።

በአንደዚህ ዓይነት የሪፎርም ሲካሄዱ ነገሮች smoothly ይሄዳሉ ተብሎ አይታሰብም።

ከዚህ በፊት በተቋማዊ የፍትሕ አካላት ( institutional law enforcing bodies) ላይ ሙሉ እምነት ያልነበረው የወጣት ቡድን ዛሬም በመንጋ ፍትሕ እየደገመው ይገኛል። ይህ ደግሞ የሚፈታው የጸጥታ እና የፍትሕ አካላትን ገለልተኛ በማድረግ ያላቸውን ቅቡልነት መጨመር ነው።

ግን የዚህ ሪፎርም የመጨረሻ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል?
ሦስት ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ።

፩. የቀድሞው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይነት ላይ ያነጣጠረ እርምጃዎች መወሰድ። ይህ ዴሞክራሲን ለማስፈን እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሲባል የሚወሰዱ እርምጃዎችን ያመለክታል። ዋናው ዐላማውም ሥልጣን እና የምጣኔ ሃብት የበላይነት ማስቀረት ነው። የበላይነቱን ለማስቀጠል የሚጠቀሙበትን ተቋማት እና አሠራሮችን በሕግ ከለላ መምታት (የጸጥታ፣ የፍትሕ እና የአስፈጻሚ አካላት ሪፎርም፣ የገንዘብ ዝውውር፣ የኢኮኖሚ እና የጉምሩክ አሠራር ሪፎርም ማድረግ) ይጠቅበታል።

የለውጥ ኃይሉ ማኅበራዊ መሠረቱን ለማጠንከር የሥራ እድል ፈጠራ፣ አዳዲስ ሃገራዊ ፕሮጀክቶችን መጀመር እና ስትራቴጂካዊ ዲፕሎማሲዎችን ማካሄድ።

በተጨማሪም ከቀድሞው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይ ቡድን ጋር ድርድር እና ሥምምነት ያስፈልጋል። የነሱን ንበረት እና ደኅንነት ከመንጋ ቁጣ (angry mass) መጠበቅ ያስፈልጋል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በሕግ ተጠያቂነትን ማስፈን እንጅ እንደ reactionary ማስቀመጥ እና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲያስፈልጉ አንስቶ ማብጠልጠሉ scapegoating ይሆናል። 

በነገራችን ላይ reactionaryንመናቅ ጥሩ አይደለም። ማንንም ጠቅሞ የትኛውም ሪቮሉሽን ከchronic reactionary ዘላቂ ጥቅም አግኝቶ አያውቅም። ስለዚህ እውነተኛው ፍትሕ፣ የምሕረት እና እርቅ ሳይዛነፍ መተግበሩንም ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ፍትሕ እና ምሕረት ካልተመጣጠነ የመንጋ ፖለቲካ ምንጭ ተዓማኒነቱን ይገዳደረዋልና።

እንደዛ ካልሆነ ሁለተኛው ክስተት ሊመጣ ይችላል።

፪. የለውጥ ኃይሉን እላማ ያደረጉ፣ የለውጡን ፍሬ ከንቱ የሚያደርጉ እና በእንጭጩ የሚቀጩ እንቅስቃሴዎች ከቀድሞው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላዮች ይሠነዘራሉ። የዓለምን ማኅበረ ፖለቲካ ፍቅር አይገዛም። ጥቅም እናን ሕግ እንጂ።

ጥቅሙ የተነካበት አናሳው ፈርጣማ የድርድር ጣሪያው ከፍ አድርጎ ይገዳደርሃል፣ ባለው የጸጥታ ውስጥ ረጅም እጅ advantage ሠላም ይነሳሃል፣ መንጋውን በገንዘብ ደልሎ ያምስሃል፣ በነበረው የበላይነት ያካበተውን ወዳጅነት ተጠቅሞ የጎረቤት ሃገሮችን እና ወሳኝ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድህ ላይ ውሃ ይቸልሳል፣ በዚህም ተዓማኒነትህን በሃገር ቤት፣ ገጽታህን በዓለም ፊት ገደል ይከታል…ከዚያም ተመልሶ ይንሰራራል። Don’t corner that cat, if you don’t want to be back to square one.

Rather give a milk it licks where you own the cow.

አለዚያ ሳትዘጋጅ ሦስተኛው ክስተት ይከሰታል

፫. ግጭት (Violence)

ተቋማዊ ቁመና እና ግልጽ ሕጋዊ ማእቀፍ የሌለው መደመርህ እንዲሁም በጥቂት በጎ ፈቃደኞች የሚመራው ቡድንህ ከአቅም በላይ ሥርዓት አልበኝነት፣ ይገጠመውና፣ ተዓመኒነትህ ይሸረሸርና፣ ያቆሰልከው አውሬ ያገግምና ራስህን ለማትረፍ ስትል “ኃይል የተቀላቀለበት” አብዮታዊ እርምጃህን መልሰህ ትቀዳጃለህ…ኢሕአዴግ ትሆናለህ…ጥልቅ ተሓድሶ ትላለህ…ለሕዝቡ መልስ አልሰጠህም፣ ኢኮኖሚው ይወድቅና ሥራ አጥነት ሥራ ይሆንና… (አያምጣው)።

መፍትሔ፦ የራ ቁጥር አንድን ደግመክ አንብብ።

In addition remember this: “DON’T CORNER THAT CAT”.

No comments