Latest

የ"ለምን?" ጥያቄ (በላይ በቀለ ወያ)

የ"ለምን?" ጥያቄ (በላይ በቀለ ወያ)


የ"ለምን?" ጥያቄ 

(በላይ በቀለ ወያ)

ሀገር ሀገር ስንል ፣ ለምን ሀገር አጣን
ምስጢሮች ስንሆን ፣ ለምን ገሀድ ወጣን?

የምንወዳቸው ፣ ለምን ይጠሉናል
የተደበቅናቸው ፣ ለምን ያገኙናል
ያቆምናቸው ሁሉ ፣ ለምን ይጥሉናል?

አንድነት ነው ያልነው ፣ ለምን ተለያየ
ለምን የሰወርነው ፣ በመገለጥ ታየ?

ቆይ ለምን ጨለመ ፣ ይነጋል ያልነው ቀን
የረሳነው ሁሉ ፣ ለምን ሲል ናፈቀን
ንቀን የነቀፍነው ፣ ለምን አደነቀን?

ወደ አምላክ ስንጮህ ፣ ለምን ሰይጣን ሰማን
ለምን ፀድቀን ሳለ ፣ አገኘን እርግማን?

ወዛሞች ስንሆን ፣ ቆይ ለምን ገረጣን
ለምን ከዓለም ቀድመን ፣ ካለም ኋላ መጣን
ለምን ለምን ስንል ፣ ቆይ ለምን መልስ አጣን?

ለምን
ለምን
ለምን
ሚሉ ጥያቄዎች ፣
ነበሩን ለምኖች
መልሱን ያላወቅነው
ታዲያ ለምን ተውነው?

No comments