Latest

ለማመን የሚያስቸግሩ የዘጠና ቀን ተዓምራት! በክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ


ክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ "የጦር ሐይሎች አዛዥ" የሰሩዋቸውን ድንቅና ዉስብስብ እዉነቶች ።

• ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ወደ ከፍታ ማማቸው እና ዜግነታቸው መለሱ ።

• ለማመን ቀርቶ ለማለም የሚቸግረንን የነፃነት አብዩት ከፊት ሆነው መሩ ።

• ዜግነታችን የሚሰጠንን ክብር አወጁ ።

• ሽብርተኛ ተብለው የታሰሩ መሪዎችና ጓዶቻችንን በነፃ ለቀቁ ።

• በመለስ ዜናዊና በደደቢት ጓዶቹ አህያ አልብሰው የተሳለቁባትን ሰንደቃላማችንን በክብር አዉለበለቡ

• ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ከየሐገራቱ ከአረቡ ዐለምና ከአፍሪካ እስር ቤት አስለቅቀዉ እየተላቀሱ በአንድ አይሮፕላን ተሳፍረው መዲናቸዉ ይዘው ገቡ ።

• የኢትዮ ኤርትራን የድንበር ጦርነት በአለም ዐቀፍ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሰላም ቋጩ ።

• በ81 ከመቶ በአሻጥር ህዉሓት ከቻይና ጋር በመመሳጠር ልታወጣ የነበረዉን ነዳጅ ጉድጓዶች ሴራ አጋለጡ ፕሮጀክቱንም አስጀመሩ ።

• በህዉሓት በሽብርተኝነት ተፈርጀው የነበሩ የነፃነት ድርጅቶችን በሚኒስተሮች ምክር ቤት አስነሱ ።

• ተቃዋሚ የሚለውን በተፎካካሪ ቀየሩ ።

• በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል ያሉ ሐይሎችን ሁሉ ወደ እናት ሐገራቸው ጠሩ ።

• የእህት ሐገር ኤርትራን የሰላም ልዑካን ቡድን ራሳቸው ሔደው ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በክብር ተቀብለው ተወያዩ

• የአለማችን ቱጃሩን የዱባይ ልዑል ራሳቸዉ መኪና እየነዱ በቦሌ አየር ማረፊያ ተገኝተው ወደ ቤተመንግሥታቸው አደረሱ ። 3.ቢሊዮን ዶላርም ያለእርዳታ ተቀበሉ ።

• የደቡብ ሱዳኖቹን ሳልቫኪር እና ሪክ ማቻርን አስተቃቅፈዉ ሸመገሉ ።

• ከUganda ሐገር ከኔልስን ማንዴላ ቀጥሎ ታላቁን ኒሻን ተቀበሉ ።

• ከግርማዊ ጃንሆይ ቀጥሎ በአማርኛ ቋንቋ በኦፊሴላዊ ጉብኝት ወቅት ተጠቀሙ ።

• በምስራቅ አፍሪካና ቀጠናው ያለ ምንም እረፍት ተጓዙ ።

• ኢትዮጵያዊ አንድነትንና ብሔርተኝነትን ከዳር እስከ ዳር ድረስ አቀጣጠሉ ፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ተደማጭና በአንድ ፊሽካ ዜጋን የሚያዙ የተከበሩ መሪ ሆኑ ።

• የመከላከያ የፖሊስና የደህንነት ሐይሎችን ሚሊሺያዎችን በአንድ አሰለፉ ።

• የዉጪ ሐገር መሪዎችና ዲፕሎማቶችን የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ቀልብ ማርከው ገዙ ።

• ኢንተርናሽናል ሚዲያዎችን ሞገሳቸዉን አገኙ ።

• ከተቀነባበረ የጅቦች የቦንብ ጥቃት በኢትዮጵያ የሰራዊት ጌታ ተረፉ ። የለበሱትን ካኔቴራ ለፋሽን ሾዉ ሳይቀይሩ ለተጎጂዎች ደም ልገሳ ሆስፒታል ተጓዙ ።

"ዐቢይ ይህንን ሁሉ በ90 ቀን ዉስጥ ሆኗል !"

አንቱ የምንልህ ለፕሮቶኮል ያህል ነው ። መሪያችን ሆይ ስለ ሁሉም ልፋትህ እናመሰግናለን ፤ ከእያንዳንዷ እርምጃህ ጀርባ እኛ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ዜጎችህ በትጋትና በተጠንቀቅ አለን !!!

ማስታወሻ  በተጠቀሱት ለማመን በሚያስቸግሩ ተዓምራዊ ለዉጦችና እዉነቶች ላይ የቀረ ነጥብ ነገር ካለ ጨምሩበት

ኢትዮጵያ በክብር ለዘለዓለም ትኑር ! ድል የሕዝብ ነው !

No comments