"በጭናክሰን በአንድ ወር ብቻ 38 ሰው ተገድሏል፤ 25 ሰው ቆስሏል"- የወረዳው ቃል አቀባይ
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በጭናክሰንና ሌሎች ወረዳዎች የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በአራት አቅጣጫ ጦርነት እንደከፈተባቸውና ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች እንደተገደሉ ገለጹ።
"የጭናክሰን ወረዳ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ዛሬን ጨምሮ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ 38 ሰው ሲገድል 25 ሰው አቁስሏል። " ብለዋል።
"ጉርሱም ውስጥ አራት ሰው ተገድሎ ዛሬ እየቀበርን ነው" ያሉም ነዋሪ አሉ።
የሶማሌ ክልል መንግሥት "ልዩ ፖሊስ ለበጎ ሥራ እንጂ ለግድያ አይሰማራም" ሲል ማስተባበሉ ይታወሳል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
No comments