Latest

ኢትዮጵያዊነትን ያገዘፈ ኢትዮጵያዊ!!


ዶክተር ዓብይ ስልጣን በያዘ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በርካታ ስራዎች ሲሰራ ማየታችን፣ የቀደሙት መሪዎች ባሳለፍናቸው ሃያ ሰባት ዓመታት፣ ለምን በአንድ ቀለበት ሲዞሩ ኖሩ? የሚል ጥያቄ ይፈጥራል፡፡

በዓለማችን ካሉ መሪዎች ውስጥ
  • በወህኒ ቤት ተጥሎ፣ በሞት ጨለማ ውስጥ የነበረውን ታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌን ቤተ መንግስት ድረስ ጋብዞ፣ አውግቶና ሀሳቡን አድምጦ የሸኘ፤
  • ሳዑዲ አረቢያ ድረስ በመሄድ የአንዲት ኢትዮያዊት እናት ሀዘን የተጋራና የሚያፅናና፤
  • በባዕድ አገር በእስር ቤት የሚማቅቁ ወገኖችን ፍለጋ ባህር አቋርጠው፣ “ፍቱልን!” የሚል፤ 
  • እንደ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩን የመሰሉ ለሀገር ውስጥ ጋዜጠኞችና ደራሲያን ዕውቅና የሰጠና አክብሮት የሚያሳይ፡፡ 
  • “ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት” በአሮጌ ሳጥን ተቆልፎበት ዓመታት ባስቆጠረበት፣ የብዙዎች ልብ በሀዘን ተሰብሮና በትዝታ ተቋጥሮ በኖረበት ዘመን ኢትዮጵያዊነትን በንግግሮቹ ሁሉ የማይለይና ፍቅርን መሰረት አርጎ የሚመራ መሪ ከእኛው ዶክተር ዓብይ ውጭ ከየትስ ይኖራል?
ሀሳብ አመንጪነቱ፣ ለውጥ ፈላጊነቱ፣ ህይወትን ቀለል አድርጎ ማየቱና ለትውልድ መጨነቁ እውነተኛ መሪ መሆኑን ይመሰክራል

የትም ቦታ ብሄድ ከፊትሽ ብጠፋ
በሕይወት ለመኖር ባይኖረኝም ተስፋ
ባንቺ ክብር ዝና በፍቅርና ስምሽ
በህይወት ባልኖርም መጠሪያ ቅርሴ ነሽ

No comments