Latest

ስልጣን ማገልገያ እንጂ መገልገያ አይደለም:- ጠ/ሚ አብይ አህመድ


ስልጣን ማገልገያ እንጂ መገልገያ መሆን እንደሌለበት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚንስትሩ በአጭር ጊዜ ላመጧቸው ስኬቶች ዕውቅና ለመስጠትና አጋርነትን ለመግለፅ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በሰልፉ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ  ያለንን እየጣልን የሌለንን ለመፈለግ ስንባዝን ያጣነውን በፍቅር መመለስ አለብን ብለዋል።
ሰልፈኞቹን ይህ የኔ ክልል ነው ውጡልኝ መባባል አቁማችሁ በፍቅር ለአንድ ሀገር በጋራ መስራት የጀመራችሁ እለት በሌላችሁበት ምስጋናቹሁን እንደደረሰን እንቆጥረዋለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ዶ/ር አብይ ልጆቻችሁን ከፊደል ባለፈ የአገር ፍቅር እያስተማራችሁ ስታሳድጉ  ያኔ ፍሬውን እናየዋለን ብለዋል።
አላማችን ሩቅ ነው ግባችንም እጅግ በጣም ሰፊ ነው አገራችን ወደ ቀድሞ ክብሯ እንደምትመለስ ጥርጣሬ  አይኑራችሁ  ይህ እንዲሆን ግን ይቅርታ ፣ ፍቅርንና መደመርን መርህ ልናደርግ ይገባል ነው ያሉት።
የሰው ልጅ እስትንፋስ መጀምሪያ፣ የጥቁር ሰው የነጻነትና የአልበገር ባይነት ምልክት የሆነችው ኢትዮጵያ ወደ ቀደመው ክብሯ እንደትመለስ ምሁራን የበሰለ ሀሳብ አምጡ ፣ ባለሞያዎች የበሰለ ሀሳብ አምጡ፣  የሀይማኖት አባቶች ዘረኝነትንና ሙሰኝነትን አጥፋታችሁ  ድሀ ተበደለ  ፍትህ ተጎደለ ብለችሁ ድምፃችሁን አሰሙ ብለዋል።
ዶክተር አብይ እንዳሉት አገራችን ከወደድን ለሚንገላታውን እያንዳንዱ ዜጋ ልንቆምለት፣  ያለስራ ለምትባክን ለእያንዳንዷ ሰአት ልንቆረቆርላት፣ በየትኛውም የአገራችን ክፍል መብቱ ሲጣስ ማንነቱ ሳንመለከት ወገኔ ብለን ልንቆምለት ይገባል።
ላለፈው አንድ መቶ አመት ጥላቻ ሸብቦናል የኔ ብቻ የሚል ሆዳምነት ግለኝነት ጎድቶናል ይህንን በደልና ችግር አሸንፈን እንድንሻገር የሚያስችለን ፍቅርና ይቅርታ ብቻ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ።
ለአገሪቱ  እድገት ሁሉም የድርሻውን እንዲያበረክትም  ጥሪ አቅርበዋል።

No comments