Latest

በመስቀል አደባበዩ የትናንቱ ፍንዳታ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች እርዳታ ያስፈልጋቸዋል- የድጋፍ ስልፍ አስተባባሪ ኮሚቴው


በመስቀል አደባበዩ የጠ/ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በትናንቱ የቦንብ ፍንዳታ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የድጋፍ ሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ ገለጸ።

ጠ/ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባለፉት ጥቂት ወራት ባስመዝገቧቸው ለውጦች የምስጋና ሰልፍ ላይ በደረሰው ፍንዳታ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችን መጎብኘቱን የድጋፍ ሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ኮሚቴው በዚሁ መግለጫው እንዳመላከተው በድጋፍ ሰልፉ ላይ በደረሰው ፍንዳታ የተጎዱት ዜጎች ደም የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፥ ህብረተሰቡ የደም ልግሳ ትብብር ያደርግላቸው ዘንድ መልካም ትብብር ጠይቋል።

ለተጎጂዎችና ሟች ቤተሰቦችም በመንግስት በኩል የገንዘብ ድጋፈ ሊደረግላቸው ይገባል ብሏል የድጋፍ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴው።

ከአደጋው ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ተጠርጣሪዎችም አስፈላጊው ማጣራት ከተደረገ በኋላ በስቸኳይ ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው ጠይቋል።

ተጎጂዎቹ ህክምናቸውን በቀጣይነት እንዲከታተሉ ለማድረግም የሂሳብ አካውንት በመክፈት ህብርተሰቡን በማሳተፍ ለተጎጂዎቹ ገቢ የማሰማባሰብ ስራ መሰራት እንዳለበትም በኮሚቴው ተገልጿል።

የድጋፍ ሰልፉ አስተባባሪ ጠ/ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባለፉት ጥቂት ወራት ላስመዝገቧቸው ለውጦች የምስጋና ሰልፍ ላይ ለታደመው ህዘብም ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ ምስጋናውን አቅርቧል።

በይስማው ይርዳው

No comments