Latest

ደርግን የጣላዉ ኢህአዴግ አይደለም! ደርግን የጣለዉ ራሱ ደርግ ነዉ!!


"በየአረቄው ቤት እየዶለታችሁ በመንግስት ላይ ሴራ አትጠንሥሱ! ስልጣን ላይ ስለነበራችሁ ከህግ የምታመልጡ ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል!!"ሲሉ ዶክተር አብይ ማስጠንቀቃቸው።
ደርግን የጣላዉ ኢህአዴግ አይደለም! ደርግን የጣለዉ ራሱ ደርግ ነዉ!! ደርግ የወደቀዉ ከህዝብ ልብ የወጣ ጊዜ ነዉ!!
“በኢህ አዴግ ውስጥ ልዩነት አለ እየተባለ የሚወራው ነገር ምን ያህል እውነተኛ ነው?” በሚል ከተሳታፊዎች ለቀረበላቸው ጥያቄም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ ፦

ኢህአዴግ ውስጥ ትክክለኛ ለውጥና ተሀድሶ መጥቷል። ዘጠና በመቶ የሚሆነው የድርጅቱ አባላት የለውጥ ጉዞው ውስጥ ገብቶ የገባነውን ቃል ለመተግበር ቁርጠኛ አቋም ይዟል። ይቅርታ የጠየቅነውን ሕዝብ መካስ አለብን ብሎ ያምናል።በዚህ የለውጥ ጉዞ ውስጥ ያልገባውን ኃይል በሂደት እየለዬን እናጠራዋለን” ሲሉ ተደምጠዋል።

የሕዝብና የመንግስት ሀብት እንደዘረፉ የሚጠረጠሩ ሙሰኞች ለፍርድ ሊቀርቡ ነው። ሪፖርተር ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በተደራጀና በቅንጅት የሕዝብና የመንግሥት ሀብት መዝብረዋል ተብለው በተጠረጠሩ ላይ፣ ሕጋዊ ዕርምጃ ለመውሰድ ምርመራ ተጠናቋል።በተለያዩ የአሀገሪቱ ክፍሎች ከሚፈጸሙ ግጭቶች ጀርባ የእነኚህ ታላላቅ ሙሰኞች እጅ እንዳለበት ብዙዎች ያምናሉ።

በአርባ ምንጭ የዶክተር አብይን የለውጥ ጅምር ለማበረታታት የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ የጠየቁ ወጣቶች በፖሊሶች ተደብድበዋል።
ባህርዳር እና ከሃያ በላይ የአማራ ክልል ከተሞች ለታላቅ ሰልፍ ተዘጋጅተዋል።ጸረ ለውጥ ኃይሎች በእነዚህ ሰልፎች ላይ ሆነ ብለው አማራዎችንና ኦሮሞዎችን የሚያጋጩ ጽሁፎች ለማሰራጬት ስለተዘጋጁ ሕዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የሁሉእቱም ክልሎች የኮሙኒኬሽን ቢሮዎች አሣስበዋል።
ሌሎችንም መረጃዎች አጠናቅረናል። ትንሳኤን በማድመጥ የመረጃ ክፍተትዎን ይሙሉ።
ትንሳኤ- የእርስዎ ራዲዮ!

No comments