Latest

የታማኝ በየነ መልዕክት - ከእንግዲህ መለያየት የለም፤ ብዙ ቋንቋ የምንናገር ግን የአንድ ሀገር ልጆች አንድ ህዝብ ነን!!


ሰላም ለሁላችሁም
ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማቆየት ስንቶች በመርዝ ረገፉ ስንቶች በየሜዳው ሳይቀበሩ ቀሩ ስንቶች አካለ ጎደሎ ሆኑ ስንቶች ቤታቸውን ትተው ተሰደዱ ስንቶች በየእስርቤቱ ተገረፉ; ዛሬም ኢትዮጵያዊነትን በፍቅር ለማስቀጠል በተጠራው ሰልፍ ላይ ቦንብ ተወርውሮ የኢትዮጵያዊያን ደም ፈሰሰ።

በአዲስ አበባ የምትኖሩ ወገኖቼ በዚህ አደጋ ህይዎታቸውን ላጡ ቤተሰቦችም ሆነ በአደጋው የቆሰሉትን በየቤታቸው እየሄዳችሁ በእኢትዮጵያዊነት ፍቅር እንድታጽናኗቸው በአክብሮት እለምናችኋለሁ። 

ከእንግዲህ መለያየት የለም ። ብዙ ቋንቋ የምንናገር ግን የአንድ ሀገር ልጆች አንድ ህዝብ ነን በልዩነታችን ተቻችለን በፍቅር በአንድነት አብረን እንኖራለን

ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል

No comments