Latest

ቦንብ አፈንጅዎቹ 300 ሺህ ብር ቀብድ ወስደው ነበር

ቦንብ

ቦንብ አፈንጅዎቹ 500 ሺህ ብር ለያንዳንዳቸው እንደሚከፈል፣ የራሳቸው ክልል ያልሆነ መታወቂያ እንደታደላቸውና ከ 2 ቀን በፊት በፒካፕ መኪና እንደመጡ ተናግረዋል

ቦምብ በመወርወር በዶ/ር አብይ ላይ ላይ ጉዳት ለማድረስ የሞከሩት አምስት እብድ መሳይ ሴቶችና አንድ የፖሊስ ልብስ የለበሰ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ሁሉም የራሳቸው ክልል ያልሆነ መታወቂያ ይዘው እንደነበር ፖሊስ በሰበር ዜናው አስታውቋል፡፡
አምስቱም ሴቶች መታወቂያው ከ 4 ቀን በፊት መሰጠታቸውን የገለጹ ሲሆን እያንዳንዳቸው የ300,000 ብር ክፍያ እንደተደረገላቸውና ስራውን ሲያጠናቅቁ ቀሪ 200,000 ብር እንደሚሰጣቸው ቃል እንደተገባላቸውም ተናግረዋል፡፡

ግለሰቦቹ ከ 2 ቀን በፊት በ ፒክ አፕ መኪና ከ ተንበይ አዲስ አበባ መግባታቸውንም ጨምረው የተናገሩ ሲሆን ያዘዛቸውን ሰው ግን በመልክም በስምም እንደማያቁ ተናግረዋል፡፡በቀጣይ አዲስ ነገር ሲኖር ለህዝቡ እንደሚገልጹ ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል::

No comments